Benedict

Published on January 2017 | Categories: Documents | Downloads: 85 | Comments: 0 | Views: 701
of 1
Download PDF   Embed   Report

Comments

Content

የቡራኬ ጸሎት
በቤተክርስቲያን የመጨረሻው ሰዓት ጸሎት ሰዎች ቶሎ ብለው ወጥተው ወደ ተለያዩ ጉዳዮቻቸው
ማለትም ወደ ያዙት ቀጠሮ፣ ወደ ምግብ ቤት፣ ቲቪ ላይ ወደሚያዩ ፕሮግራም ወዘተ ለመሄድ
ዕቃዎቻቸውን እያሰባሰቡ የሚዘጋጁበት ጥሩ ጊዜ ሆኖላቸዋል፡፡ በጣም ጥሩ የቤተክርስቲያን አዘውታሪ ነኝ
የሚለው ሰው እንኳን የወገኖችን ዓይን ለጸሎት መከደንና የማይቆለፈውንና ሰው በፈለገው ሰዓት
የሚከፍተውን የቤተክርስቲያን በር ተጠቅሞ ወዲያው ፈትልክ ይላል፡፡ የመጨረሻው የቡራኬ ጸሎት
ደግሞ ልክ በሩጫ ሜዳ ላይ እንደሚተኮሰው ሽጉጥ በቦታ፣ ተዘጋጅ፣ እሩጥ የሚል ቅዱስ ትዕዛዝ
ይመስል ሰዎች ያንን ከሰሙ በኃላ መሄድ እንደሚችሉ የሚያውቁበት መሳሪያ በመሆን መታወቅ ከጀመረ
ዘመን አስቆጠረ፡፡
ነገር ግን ይህ የመጨረሻው የቡራኬ ጸሎት፣ መገለጥና ህይወት ያለበት ቢሆንስ ? ነገር ግን
መንፈስ ቅዱስ የሚሰማ ጆሮ ላላቸው ሰዎች ህይወታቸውን የሚለውጥ መገለጥ የሚለቅበት ቡራኬ
ቢሆንስ!
አንድ ህይወት ሰጭ የሆነ ዓይንን የሚከፍት የቡራኬ ጸሎት በይሁዳ መልዕክት መጨረሻ አካባቢ
ላይ ተቀብሮ ከብዙዎቻችን ተሰውሮ እናገኘዋለን፡፡

ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃሁ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ በፊቱ እንዲያቆማችሁ
ለሚችለው ብቻውን ለሆነ አምላክና መድሃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከዘላለምም ድረስ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን› ይሁዳ.24-25
በዚህች አጭር የመሰናበቻ መልዕክት ውስጥ 3 በጣም ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን እናያለን፡፡
1. እንዳንወድቅ ሊጠብቀን የሚችል፡- ይሁዳ እዚህ ጋር የሚያሳስበን ከእግዚአብሄር ታላቅነት አንዱ የሆነው
እኛን ከበደል የሚያነጻ እምላክ ብቻ ሳይሆን እንዳንወድቅም ሊጠብቀን መቻሉም ጭምር ነው፡፡ ከርሱ
ጋር መራመድ ማለት ፈጽሞ እንደማይወድቅ ዓይነት ሰው መሆን ማለት እንደሆ እናምን ይሆን ?
የተፍገመገመው ያልወደቀው ጠንካራ ስለሆነ ሳይሆን ጠባቂ ስላለው ነው፡፡
2. ነውር የሌላቸው አድርጎ በፊቱ የሚያቆመን፡- ሳንሰናከል መራመድን መማር እንዳለብን ሁሉ
በምንሰናከልባቸው ማንኛውም ጊዜያቶች ሁሉ ግን ሊደግፈንና ሊያነጻን እግዚአብሄር ከጎናችን አለ፡፡
ሁላችን በፊቱ ልንቆም የሚገባን ቀን እየመጣ ነው፡፡ በጣም ደስ የሚያሰኘው ደግሞ ያለነውር አድርጎ
ለዚያ ቀን የሚያበቃንም እርሱ እራሱ ነው፡፡
3. በታላቅ ደስታ፡- ዛሬም እንደ ሌላው ቀን ሁሉ ለኢየሱስ ደቀመዛሙርት ደስ የሚሰኝ ቀን ነው፡፡
የህይወታችን ፍጻሜ የሚሆነው በደስታ ነው፣ እንዲያውም በታላቅ ደስታ፡፡ ፍጸሜዬ ይኼ ከሆነ ምን
አስጨነቀኝ በእያንዳንዷ እርምጃዬ ደስታዬን እያበዛሁ መሄድ ነው እንጂ፡፡
የነዚህ የሦስቱ ድንቅ ዕውነቶች ጀማሪውና ፈጻሚው እነዚህ ነገሮች በህይወታችን ሳይከለከሉ
እንዲሆኑ ያደርግ ዘንድ ክብርና፣ ግርማ፣ ኃይልም፣ ስልጣንም ያለውና የተሞላው እግዚአብሄር ነው፡፡
ይሁዳም ይህን በረከት በርግጥ እንደምናገኝ ተስፋ ይሰጠናል ታዲያ ለመጨረሻው የቡራኬ ጸሎት
መገኘት አለብን ቸኩለን አንውጣ፡፡ እኛም በየቤተክርስቲያኑ ቡራኬ የምናደርግ ጌታ በስፍራው
ያስቀመጠን ሰዎች ከተለምዶ ወጥተን ህይወትን በሚነካና በሚለውጥ ነገር ላይ ትኩረት እናድርግ፡፡
ለዛሬ ግን ይህን የቡራኬ ቃል የተናገራችሁ የጌታም ወንድም የሆነው ይሁዳ ነው፡፡

Sponsor Documents

Or use your account on DocShare.tips

Hide

Forgot your password?

Or register your new account on DocShare.tips

Hide

Lost your password? Please enter your email address. You will receive a link to create a new password.

Back to log-in

Close